info@coffeesspices.gov.et | +251 46 221 0000
Announcements

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሉዕክ የቻይና-ኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የቡና ንግድ ማስተዋወቂያ ኮንፍራንስ ላይ በመካፈል ላይ ይገኛል

December 28, 2025 10 Views
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሉዕክ የቻይና-ኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የቡና ንግድ ማስተዋወቂያ ኮንፍራንስ ላይ በመካፈል ላይ ይገኛል
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ሉዕክ የቻይና-ኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የቡና ንግድ ማስተዋወቂያ ኮንፍራንስ ላይ በመካፈል ላይ ይገኛል

ሉዕኩ በቻይና ሁናን ቆይታው፤ በኢትዮ-ቻይና የወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ አስተባባሪነት እንዲሁም በሁናን ዡዡ ከተማ (Hunan, Zhuzhou City) እና በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አዘጋጅነት በጋራ በተዘጋጀ የመጀመሪያው የቻይና-ኢትዮጵያ የኢኮኖሚና የቡና ንግድ ማስተዋወቂያ ኮንፍራንስ እና ሌሎች ፕሮግራሞች ላይ በመካፈል ላይ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከኢትዮ-ቻይና የወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ ጋር በንግድና ገበያ ትስስር፤ በኢንቨስትመንት፤ በአማራጭ ታዳሽ ኃይል፤ በኢ-ተሽከርካሪዎች አቅርቦት እና በሌሎች ተያያዥ የኢኮኖሚና የልማት ትብብሮች ዙሪያ ተከታታይ ውይይቶችን በማድረግ ውጤታማ የትብብር ማዕቀፍ መፍጠራቸው ይታወቃል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይ ትብብሩን ወደ ቋሚ ስትራቴጂያዊ የልማት አጋርነት በማሳደግ፤ የክልሉን የቡና ምርት በቻይና ገበያዎች የማስተዋወቅና ኤክስፖርትን የማሳደግ እንዲሁም የቻይና ባለሀብቶችና ካምፓኒዎች በተለያዩ የንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች በማሳተፍ የክልሉን ልማት እንዲደግፉ ለማስቻል ሲሰሩም ቆይተዋል፡፡

በዚህም የክልሉ መንግስት ስትራቴጂያዊ የሦሥትዮሽ የቀጥታ የንግድ ልውውጥና ትብብር የጋራ መግባቢያ ስምምነት ከሁናን ዡዡ ከተማ እና ከኢትዮ-ቻይና የወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ ጋር መፈራረሙ ይታወሳል፡፡

የዚሁ ስምምነት አካል በሁናን ዡዡ በተዘጋጀው የመጀመሪያው የቻይና-ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና የቡና ንግድ ማስተዋወቂያ ኮንፍራንስ ላይ እየተካፈለ የሚገኘው ልዑክ ባለፉ ጊዜያት በተደረሱ ስምምነቶች መሠረት የይርጋጨፌን ባለልዩ ጣዕም ቡናን ጨምሮ የክልሉን የቡና ምርት በማስተዋወቅ የገበያ ትስስሩን የሚያጠናክርና የሚያሰፋ ይሆናል፡፡

ከዚህም ባለፈ ልዕኩ የክልሉን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም ለቻይና ባለሀብቶች እና ካምፓኒዎች በማስተዋወቅ የክልሉን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚሰራ ሲሆን፤ ተጨማሪ የኢኮኖሚ፤ የንግድና የልማት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቶችንም ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለተከታታይ አራት ቀናት የሚካሄደው ኮንፍራንሱ የኢንትርፕራይዞችና ኢንዱስትሪዎች ጉብኝት፤ የክልሉን የቡና ምርት ማስተዋወቂያ እና የኢኮኖሚና የንግድ ትብብር ማጠናከሪያ የምክክር መድረክን ጨምሮ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን ያካተተም ነው፡፡

በመርሃ ግብሩ ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በተጨማሪ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ በክልሉ የሚገገኙ አመራሮች ተገኝተዋል።

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት
Share this article: